አምንስቲ የአዉሮፓ ለሊቢያ ስደተኞች በሚል የሚያደርገውን ድጋፍ ድጋሚ እንዲያጤን ጠየቀ፡፡


ስደተኞች በሊቢያ 
አዉሮፓ ለመግባት ሲጓዙ ተይዘዉ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ የተገደዱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሊቢያ መባረራቸዉን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አጋለጠ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ስደተኞቹ ከባሕር ላይ እየተያዙ ወደ ሊቢያ ከተመለሱ በኋላ የተለያዩ ታጣቂዎች  በሚቆጣጠሯቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲሰፍሩ ተገድደው ነበር ብሏል።

በአብዛኛዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕዉቅና ከሰጠዉ የሊቢያ መንግስት ጋር የሚተባበሩት ታጣቂዎች ስደተኞቹን ያለምንም የሕግ ሂደት ከየመጠለያ ጣቢያዉ እያስወጡ አባርዋቸዋል።

እንደ አምንስቲ መረጃ መንበሩን ምስራቃዊ ሊቢያ ያደረገዉ የሊቢያ ምክር ቤት ተባባሪ ታጣቂዎችም በርካታ ስደተኞችን አባረዋል።

ድርጅቱ እንደሚለዉ ካለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ እስከ መስከረም መጀመሪያ በነበሩት ሁለት ሳምንታት ዉስጥ ብቻ ልጆችና ሴቶችን ጨምሮ 8 ሺህ 500 ስደተኞች ወደ አዉሮፓ ሲጓዙ ባሕር ላይ እየተያዙ በግድ ወደ ሊቢያ ተወስደዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 ወዲህ 60 ሺህ ስደተኞች የሜድትራኒያን ባሕርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ እየተያዙ ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል።

የአዉሮፓ ህብረት ወደ ግዛቱ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞችን የሊቢያ ጠረፍ ጠባቂዎችና ሌሎች ኃይላት እየያዙ ወደ ሊቢያ እንዲመልሱለት ከታጣቂዎቹ ጋር ተዋዉሏል።

አምስቲ ኢንተርናሽናል የሕብረቱን አቋምና ርምጃን አዉግዞታል። ስደተኞቹ ከሊቢያ የተጋዙበትን ሐገር ወይም ሥፍራ ዘገባዉ አልጠቀሰም።

አብዛኞቹ ስደተኞች የአፍሪና የአረብ ሐገራት ዜጎች ናቸዉ።


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments