አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከዚህ ቀደም ታስረውበት ወደ ነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገለፁ።
እንደ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ከሆነ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌላ አንድ
ግለሰብም ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ላይ አቃቤ ሕግ የፀረ ሽብር አዋጅን በመተላለፍ ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
በፖለቲከኛውና ጋዜጠኛው አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የቀረቡት ክሶች ኃይልን በመጠቀም መንግሥትን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራን የሚጠቅሱ ናቸው።
ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ እስክንድር
ላይ ክስ መመስረቱን ያስታወሱት ጠበቃው፤ ፍርድ ቤቱም ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ማዘዙን ጠቅሰዋል።
ቢቢሲ
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን