የኦሮሚያ የዓፋርና የሃረሪ ክልል ርእሳነ መስተዳድሮች በመተሐራ የጎርፍ ተጎጂዎችን በአፋጣኝ እንደግፋለን አሉ።



መተሐራ በሚገኝ ሃርዋዲ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች
የኦሮሚያ የዓፋርና የሃረሪ ክልል ርእሳነ መስተዳድሮች በመተሐራ የጎርፍ ተጎጂዎችን በአፋጣኝ እንደግፋለን አሉ።

የሶስቱም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች በመተሐራ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት በከተማውና በወረዳዎች ስለደረሰው ጉዳትና ቅድመ መከላከል ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

በማብራሪያውም በአዋሽ ወንዝ ሙላት በ4 ወረዳዎች 10ሺህ ሰዎች ቤት ንብረታቸው ወድሞ መፈናቀላቸው ተገልጿል።

በመተሐራ ከተማ ደግሞ የበሰቃ እና አዋሽ ወንዝ ሙላት 5919 አቦወራዎች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሞ በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለዋ።

በጎርፍ አደጋው ምክንያት በከተማዋ ውሃና መብራት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። ውሃ ከሌሎች ቦታዎች በቦቴና በጀሪካን እየመጣ እንደሆነም ተገልጿል።

መተሐራ በሚገኝ ሃርዋዲ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ችግር ላይ መሆናቸውንና የምግብ እጥረት መኖሩን ተናግረዋል።

መንግስት ቋሚ መጠለያቸውን እንዲገነባላቸውም ጠይቀዋል።

መተሐራ በሚገኝ ሃርዋዲ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች
በቦታውም ከ1ዓመት በታች ህፃናትን ጨምሮ፤ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞች በትምህርት ቤቱ ክፍሎች እንዲሁም ሸራ ዘርግተው እየኖሩ ነው።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉዳዩ ላይ ከዋልታ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ አደጋው ከተከሰተ 15 ቀን እንደሆነውና ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች ድጋፍ መደረጉን ድጋፉም ቀጣይ እንደሆነ ተናግረዋል።

የቆቃ ከልክ በላይ መሙላት ችግሩ እንዲፈጠር አድርጓል ያሉት ሽመልስ ለአርሶ አደሮች በልዩ ሁኔታ ድጋፍ እንደሚደረግና በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ቀድመን እንሰራለን ብለዋል።

የዓፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወሉ አርባ በዓፋር ተመሳሳይ ጉዳት መድረሱን ጠቅሰው "ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልነው ነው" ብለዋል። "ችግሩን በጋራ እንወጣዋለን። ሲሉም ነው የተናገሩት። የዓፋር ህዝብና መንግስት አብሯችሁ ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ የዓፋርና የሃረሪ ክልል ርእሳነ መስተዳድሮች በመተሐራ
የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ "የመተሐራ ሕዝብ ችግሩን በጋራ ለማለፍ ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

"የወረዳውና የክልሉ መንግስት ከህዝብ ጎን በመቆም ችግሩን በራስ አቅም ለመፍታት ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ" ሲሉም ገልፀዋል።

የሐረሪ ክልል ህዝብና መንግስት በሶስት ቀናት ውስጥ ለተጎጅው ህዝብ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments