ከሰሃራ በታች የሚኖሩ 67 ሺህ ህፃናት በረሃብ ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ተባለ፡፡
በተባበሩት
መንግስታት ህፃናት
አድን ድርጅት ሴቭ ዘችልድረን በየቀኑ በአማካኝ 426 ህፃናት ለሞት የሚያጋልጥ አደጋ እየገጠማቸው ነው ብሏል፡፡
አናዶሉ
የዜና ወኪል በተባበሩት
መንግስታት ህፃናት
አድን ድርጅት ሴቭ ዘችልድረንን ጠቅሶ እንዳስነበበው የተያዘው የፈረንጆች ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ 67 ሺህ
ህፃናት በረሃብ ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡
ዘንድሮ
በአፍሪካ የምግብ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ መከሰቱን የጠቀሰው አናዶሉ ጎርፍ፣ የምግብ ዋጋ በእጅጉ መናርና የአንበጣ መንጋ ጥቃት
በርካቶችን አፈናቅሎ ለአደጋ አጋልጧቸዋል ተብሏል፡፡
በተባበሩት
መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት ሴቭ ዘችልድረን በየቀኑ በአማካኝ 426 ህፃናት ለሞት የሚያጋልጥ አደጋ እየገጠማቸው
ነው ብሏል፡፡ በመሆኑም አፋጣኝ ድርጊታዊ መፍትሔ ካልተወሰደ ችግሩ የከፋ ይሆናል ሲልም አስጠንቅቋል፡፡
ከሰሃራ
በታች ከተከሰቱት የአንበጣ መንጋ፣ የጎርፍ አደጋ፣ የኑሮ ውድነትና የምግብ እጥረት በተጨማሪ ዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ
የአደጋው ስጋት የከፋ እንዳደረገው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
በዚህም
ሳቢያ ምጣኔ ሃብት ተቃውሶ ህፃናት የጤና አገልግሎት እንዳያገኙ እያደረጋቸው መሆኑን የህፃናት
አድን ድርጅት ሴቭ ዘችልድረንን ጠቅሶ አናዶሉ ዘግቧል፡፡
የኮሮና
ቫይረስ ወረርሽኝ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ላይ በሚያደርሰው ጫና ምክንያት የድህነት መጠኑ በ23 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል ተተንብዮ
እንደነበርም ተገልጿል፡፡
ሴቭ
ችልድረን በየቀኑ በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ህመም ምክንያት ወደ ክሊኒኮች እየመጡ ነው፤ ይህም ገና ጅምር ነው ብሏል፡፡
ክሊኒኮች
እስኪሞሉ መፍትሔ ካልተሰጠ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ህይወታቸውን ያጣሉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡
ተቋሙ
እስከ 2030 የፈረንጆቹ አቆጣጠር ድረስ 433 ሚልዮን ህፃናት በምግብ እጥረት ይጠቃሉ ብሏል፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን