በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፤ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል! ዛሬ 6 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤም ሲ በደረሰ የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን 856 ሺ 620 ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን አል አይን ዘግቧል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ አደጋው ከዚህ በላይም ጉዳት ሊያደረስ ይችል እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በዚህም ከ 48 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረትን ከውድመት መታደግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ አደጋውን ለመቆጣጠር አራት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መፍጀቱን ያነሱት አቶ ጉልላት አምስት የአደጋ ሰራተኞች በሥራ ላይ ሳሉ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡ ከ70 በላይ የአደጋ መከላከል ሰራተኞችና ከ14 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። 

አል ዐይን እንደዘገበው


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments