በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ ነው፡፡


ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮሮና ቫይረስ የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር ካለፈዉ ነሐሴ፣ የመስከረሙ ሲቀንስ ባጠቃላይ ግን እየጨመረ ነዉ።

የጤና ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ እስከ ትናንት ማታ ድረስ በነበረዉ 24 ሰዓት ዉስጥ ምርመራ ከተደረገላቸዉ 8 ሺህ 551 ሰዎች መካከል ከ660 የሚበልጡት በቫይረሱ ተይዘዋል። 14 ሰዎች ሞተዋል።

ባለፈዉ ነሐሴ በቀን እስከ 1800 የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉን የስታትስቲክስ መረጃ ያመለክታል። የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀ ካለፈው ዓመት ሚያዚያ ጀምሮ የጤና ሚንስቴር ምርመራ ያደረገዉ ለ 1 ሚሊዮን 226 ሺህ 297 ሰዎች ብቻ ነዉ። ከነዚህ መካከል 71 ሺሕ 83ቱ በቫይረሱ መያዛቸዉ ተረጋግጧል። የጤና ሚንስቴር እንደሚለዉ እስካሁን ቫይረሱ ያለባቸዉ ሰዎች ቁጥር 40 ሺህ 887 ነዉ። ከ29 ሺህ 250 በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል። የሮይተርስ ሰንጠረዥ እንደሚያመለክተዉ በኮሮና ቫይረስ በርካታ ሕዝብ ከተያዘባቸዉ 50 ሐገራት ዉስጥ ኢትዮጵያ 48ኛ ናት። ከአፍሪካ ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮና ግብፅን ተከትላ ኢትዮጵያ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments