የባሌ ዞን ቱሪዝምና የመንገድ ብልሽት



የሱዳን ባለሃብቶች ልዑክ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ባለ ሃብቶቹ በዞኑ ስለሚገኙ የቱሪዝም ዘርፍ የመዋዕለ ንዋይ አማራጮች ላይ የመስክ ምልከታ እያደረጉ ነው።

ማክሰኞ ዕለት ዲንሾ ፓርክንና ከዲንሾ 16ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ሃቤራ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎብኝተው ስለ ቦታዎቹ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

በዛሬው ቀንም(ረቡዕ) ሳነቴ፣ ሃረናንና ደሎ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተዋል።

ዋልታ ያናገራቸው ባለ ሃብቶች የዞኑ መልከዐ ምድር ምቹ ቢሆንም የመንገድ ግንባታው ጥራት መጓደል ለኢንቨስትመንት መሰናክል ነው ብለዋል።

ዋልታ ባደረገው ምልከታ ላይ ተሽከርካሪዎች በመንገድ መበላሸት ምክንያት 16 ኪሎሜትር ርቀር ለመጓዝ እስከ 1፡30 ያህል ጊዜ ይወስዳል።

በባሌ ዞን ሪራ የሚኖሩ የሚኖሩና በአካባቢው የትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች በመንገዱ መበላሸት ምክንያት ተሽከርካሪዎች በየ መንገዱ ለማደር እየተገደዱ ነው ብለዋል።

ህመምተኞችን የሚያጓጉዙ አምቡላንሶች በዚሁ መንገድ መበላሸት ሳቢያ የሰው ህይወት እንደሚያልፍባቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

አካባቢውን የሚጎበኙ የውጭ ሃገር ዜጎችም እየተንገላቱ እንደሆነ ነው ነዋሪዎቹ የገለፁልን።

በስፍራው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በመንገዱ መበላሸት ምክንያት ቆመው ተመልክተናል።


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments