ቀሳውስት የመስቀል በዓል ላይ ወረብ ሲያቀርቡ /AS pictures

ቀሳውስት የመስቀል በዓል ላይ ወረብ ሲያቀርቡ /AS pictures

     መስቀል

በአብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መሣሪያ መስቀል ተብሎ ይጠራል።ክሮስየሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተወሰደው ክሩክስ ከሚለው የላቲን ቃል ነው። ሆኖም የመስቀል አምልኮ ከክርስቶስ ዘመን በፊትም ጀምሮ የነበረ ለመሆኑ በርካታ የጽሑፍና የሥነቁፋሮ ማስረጃዎች አሉ። 

                       በዓለ መስቀል

በክርስትና ኃይማኖት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የተሰቀለበት መስቀል በአይሁድ ከተቀበረበት ሥፍራ መገኘቱን ማስታወሻ በዓል ሲሆን በምዕራብም ምሥራቅም አብያተ ክርስቲያናት ይሄንን መታሰቢያ መስከረም ቀን ሲያከብሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በየዓመቱ መስከረም ፲፯ ቀን ታከብራለች። 

"መስከረም ባበባው ሠርግ በጭብጨባው ይታወቃልይላሉ አበው። አንድም መስከረም ርዕሰ ዓውደ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በመሆኑ ወርኃ አደይ ወወርኃ ጽጌ ተብሏል። እናም ኢትዮጵያውያን በርዕሰ በዓልነት ታላቅ ማዕዘን ላይ ያስቀመጡት ወርኃ መስከረም፣ ኃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አቅፏል። ከነዚህም ውስጥ ከዕንቁጣጣሽ በዓል ቀጥሎ በሠፊው የሚታወቀው በዓለ መስቀል የተባለው ነው።

AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments