ዋትስአፕ መተግበሪያ አንድ መልእክት ከአምስት ጊዜ በላይ እንዳይላክ ከልክሏል፡፡



ክልከላው ተግባራዊ ሆነው ሃሰተኛ ወሬዎችና አሉባልታዎች እንዳይዛመቱ ነው ተብሏል፡፡

በፌስቡክ ኩባንያ ከሚተደዳደሩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መካከል ዋትስአፕመተግበሪያ አንዱ ነው፡፡

በዓለም 1ቢልዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ይህው መተግበሪያ ህንዳውያን 200 ሚልዮን የተጠቃሚዎች ቁጥር ቀዳሚውን ድርሻ ይዘዋል፡፡

ተጠቃሚዎች ምስሎችን፣ ፅሑፎችን፣ ድምፆችን እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በመጠቀም መልእክታቸውን እንዲለዋወጡ በሚያስችለው በዚሁ የማህበራዊ ትስስር ገፅ አማካኝነት የሃሰት ወሬዎች እና አሉባልታዎች በፍጥነት እየተዛመቱ በመምጣታቸው ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
የዚሁ ግጭት ቀዳሚዋ ገፈት ቀማሽ ደግሞ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች ያሏት ህንድ ናት፡፡

ከስድስት ወራት በፊት መተግበሪያውን በመጠቀም በተሰራጩ አሉባልታዎች ምክንያት የእርስ በእርስ ግጭት ተነስቶ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ የሚገኙ ተጠቃሚዎች አንድን መልእክት 20 ጊዜ ማስተላለፍ ይችሉ እንደነበር አሁን ግን ከአምስት ጊዜ በላይ እንዳያስተላልፉ ተደርጓል፡፡

ሙከራው ለስድስት ወራት ተግባራዊ ተደርጎ ከተጠና በኋላም በመላው ዓለም በሚገኙ ተጠቃሚዎች ላይ ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

መልእክቶችን በማስተላለፍ ተወዳጅነትን ያተረፈው መተግበሪያው የተሳሳቱ መረጃዎችን እና አሉባልታዎችን ለመቆጣጠር ገደቡ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን  የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ሰኞ እለት ገልፀዋል፡፡

ውሳኔው ከዋትስ አፕ በተጨማሪ ፌስ ቡክ ላይም ተግባራዊ እንዲደረግ አስተያት ሰጪዎች መናገራቸውን ቢቢሲ፣ ጋርዲያን እና ሲጂቲኤን ዘግበዋል፡፡



Post a Comment

0 Comments