![]() |
| Radio Tamazuj |
እስካሁን አምስት ጋዜጠኞች በማይታወቅ ስፍራ የታሰሩ ሲሆን ሌሎች በርካታ ጋዜጠኞች ታስረው እየተፈቱ ነው ተብሏል፡፡
ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በዳቦ እጥረት እና በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ቅር የተሰኑ ሱዳናውያን አሁንም ቁጣቸውን በየ አደባባዩ እየገለፁ ነው፡፡
እንዲህ አይነቱ ተቃውሞ አዲሷ ያልሆነው ሱዳን ለተቃውሞው ዘላቂ መፍትሔ ባለመውሰዷ ተቃውሞው መልኩን ቀይሮ ስልጣን ይብቃ ወደሚል ተውጧል፡፡
ሱዳንን ካለፉት 29 ዓመታት ወዲህ ጀምሮ በፕሬዝዳንትነት እየመሯት ያሉት ኦማር አልበሽር ህዝባቸው ስልጣን እንዲለቁ ከጠየቃቸው አንድ ወር አልፏል፡፡
በአንፃሩ ፕሬዝዳንቱ ስልጠን ላይ እንደሚቆዩ መግለፃቸውን ተከትሎ ተቃውሞው እየበረታ መጥቷል፡፡
ይህን የህዝብ ተቃውሞ እየተከታተሉ የሚዘግቡ የህገሪቱ ጋዜጠኞች ችግሩን አባብሰውታል በሚል ቅድመ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብሏል ዘ ጋርዲያን በዘገባው፡፡
ዘገባው እንደሚያሳው እስካሁን አምስት ሪፖርተሮች በሃገሪቱ ደህንነት ታግተው ወደ ማይታወቅ ስፍራ ተወስደዋል፡፡ ሌሎች በርከት ያሉ ጋዜጠኞች ታስረው እየተፈቱ ነው ተብሏል፡፡
ሁለት በዓረቢኛ ቋንቋ የሚሰሩ የዜና ጣቢያዎችም ፈቃዳቸው ተሰርዞ በሃገሪቱ እንዳይሰሩ ተከልክለዋል፡፡
እንደ አልጀዚራ ያሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም በሃገሪቱ ዘገባ እንዳይሰሩ ፈቃዳቸው ተሰርዞባቸዋል::
ካሊድ አህመድ የተባለ ጋዜጠኛ የሱዳን መገናኛ ብዙሃን በታፈኑ ቁጥር ተቃውሞው እየባሰ ሄዶ ከባድ ችግር እንደሚፈጥር እሙን ነው ሲልም ተናግሯል፡፡
ሃገሪቱ በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ረገድ ከ180 ሃገራት ከስድስት ሃገራት ብቻ ተሸላ 174ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ዘጋርዲያን
https://cpj.org/2019/01/as-anti-bashir-protests-continue-sudan-revokes-cre.php
https://cpj.org/2019/01/as-anti-bashir-protests-continue-sudan-revokes-cre.php

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን