የመሬት ናዳ በሚጢቾ |
በመሬት ናዳው ሶስት ህጻናትን ጨምሮ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላት በናዳው ተቀብረው ህይወታቸው ሲያልፍ በሌሎች ሁሉት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን የጽህፈት ቤት ኃላፊው ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሁለት መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ 14 የቀንድ ከብቶች ፣ 10 በግ ፣ 7 ፍየሎች በናዳው ሲሞቱ በማሳ ላይ የነበረ የአንሰት ተክል መውደሙንም ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አደጋው በደረሰበት ዙሪያ የሚገኙ 123 ነዋሪዎች አካባቢውን በመልቀቅ ወደ ሌላ መንደር እንዲዛወሩ መደረጉንም ተናግረዋል ።
ለመሬት ናዳው መከሰት በአካባቢው እየጣለ ከሚገኘው ዝናብ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ የጠቀሱት አቶ ተካ በቀጣይ ተመሳሳይ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ በተለይ በከፍታማ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን