እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ተወሰዱ

ላንድማርክ ሆስፒታል


እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ሃምዛ ቦረና ዛሬ ጥዋት ላንድ ማርክ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን አሳውቋል። 

ትላንት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአቶ ጃዋር ፣ አቶ በቀለ ፣ በአቶ ሀምዛ እና አቶ ደጀኔ የህክምና ጉዳይ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ቀደም ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል እንዲወስዱ ትዕዛዝ መስጠቱን ይታወሳል። 

በረሃብ አድማ ከ30 ቀናት በላይ የሆናቸው እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬ ጥዋት በገቡበት በላንድ ማርክ ሆስፒታል አከባቢ ከፍተኛ የጸጥታ ሀይል እንደተሰማራ ተዘግቧል። 




AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments